አስማት
ጎጃሞች በአስማት ተግባር እውቅ ነበሩ ይባላል:: አለቃ ተክለ ኢየሱስ እንደ ጻፉት በጎሹ ዘመን የተፈጸመ ለማመን የሚያስቸግር አንድ አስደናቂ ታሪክ አለ:: አለቃ አርአያ የሚባል አስማተኛ ይልማ አማኑኤል ከሚባል አገር ጎጃም ውስጥ ይኖር ነበር:: የውላ ከሚባል አገር የአንድ ሰው ሚስት በውሽምነት ይዞ አስማት እየደገመ ማታ ማታ ወደ ቤቱ ያመጣት ነበር:: አንድ ቀን አውሬ እንዳይበላት የሚከላከለውን ድግምት ሳይደግምባት ቀርቶ በጭለማ ወደ አለቃ አርእያ ዘንድ ስትመጣ ሳሴ ከሚባል መንደር ስትደርስ ጅብ በላት:: አባትና እናትዋ ባልዋም ሆነው ደምበጫ ሄደው ለዳጃ. ጎሹ አቤት አሉ:: ደጃች ጎሹም 'ተጩሆብሃልና መጥተህ መል

ስ ስጥ' ብለው ወደ አለቃ አርእያ መልዕክተኛ ላኩ:: አለቃ አርእያም በአስማታቸው ኮርተው አልመጣም ብለው መልስ ሰጡ::
ደጃች ጎሹም 'አስማቱ ሲያድነው አያለሁ' ብለው እጃቸውን ይዞ የሚያመጣ ጭፍራ ላኩባቸው:: ይህን ነገር አለቃ አርእያ በሰሙ ጊዜ በቤታቸው አጥር ዙሪያውን እፀ-መሰውር መድፍን አይን ደገሙና ረጩ:: ከደጃች ጎሹ የተላኩት ወታደሮችም የአለቃ አርእያን ቤት ማየት አቅቷቸው ባላገሩን ሁሉ አሳዩን እያሉ ሲገርፉና ሲያምታቱ ቆይተው ቀኑ ሲመሽ ወደ ደጃች ጎሹ ተመለሱ:: 'ከነቤቱ ተሰውሮ ጠፋብን' ብለውም ነገሩ:: ደጃች ጎሹም 'እርስ በርሳችሁ እየትስማማችሁ ነው እንጂ ቤቱ ተሰውሮ አይደለም ብለው ራሳቸው ለመሄድ ተነሱ::
የደጃች ጎሹ መኳንንትም 'ያዋርደናልና አንሂድ ባይሆን ባይሆን ታማኝ ሰው ሄዶ ይያዘው' ብለው ቢያማክሯቸው 'አይሆንም ሰውም አላምንም' ብለው ጉዞ ጀመሩ:: አማሬ ኢየሱስ ከሚባል ቦታ ሲደርሱ አለቃ አርእያ እንደመጡባቸው ሰምተው የደጃች ጎሹ ነጋሪት እንዳይጮህ ድምጽ የሚዘጋ አስማት ደገሙ:: ነጋሪት እያስመቱ መለከት እያስነፉ የሚጓዙት ደጃች ጎሹ ድንገት ነጋሪቱም የመለከቱም ድምጽ ዝም አለ:: ሰራዊታቸውም ደነገጠ:: መኳንንቱም ደጃች ጎሹ ዘንድ ቀርቦ 'ይሄን ጉድ አየን ሌላ ሳይመጣ ይህን ጊዜ እንመለስ:: በሌላ ቀን በድንገት አዘንግተን ሌሊት እንይዘዋለን' ብለው መክረው ተቆጡና ደጃች ጎሹ ተመለሱ::
ምንጭ: አጼ ቴዎድሮስ (በጳውሎስ ኞኞ)
(** ይህ እፀ-መስውር በአሁኑ በዘመናዊ ሳይንስ በፊዚክስ invisibility ይባላል:: በተለይ የአሜሪካው መከላከያ ፔንታጎን ይህንን ቴክኖሎጂ ለመጠቀምና ስራ ላይ ለማዋል ብዙ በጀት መድቦ እየሰራበት ይገኛል:: የእኛ አባቶች ግን ይህ ጥበብ ከጥንት ጀምሮ ነበራቸው...አላቸውም:: )

No comments:
Post a Comment